‹‹እና ምን ላድርግ አጎቴ? አውቶቡሶቹ ከገቡ’ኮ ስድስት ወር አለፋቸው፡፡ መጋዘኑ ውስጥ ቆመው
በከረሙ ቁጥር ዋጋቸው እየቀነሰ እንደሚሄድ ዘነጋኸው!››
የገንዘብ ሚኒስትሩ አጎቱ በዝምታ ተዋጡ፡፡
‹‹እስኪ ማታ እንገናኝና እንመካከርበት…››
***
በሳምንቱ ሼባ ሪዞርት የተባለ፣ ገና ግንባታው ያልተጠናቀቀ ሆቴል በአገሪቱ ውስጥ ካሉት አምስት
የአውቶቡስ አስመጪዎች አራቱን የአውቶቡስ አስመጪዎች ለጨረታ የዋጋ ሰነድ እንዲያስገቡ ጠየቃቸው፡፡ ይህ በሆነ በሳምንቱ ሼባ ሪዞርት
‹‹የተሻለ አማራጭ በማግኘቱ›› ጨረታውን መሰረዙን ተናገረ፡፡ ሌላ አንድ ሳምንት አለፈ፡፡
የገንዘብ ሚንስቴር ሚኒስትር፣ የአስተዳደር ክፍል ኃላፊዎችን ሰብስበው በነባሮቹ የሠራተኞች
ማመላለሻ አውቶቡሶችና፣ የሠራተኞችን ምቾት ስለመጠበቅ አዋሩዋቸው፡፡… አውቶቡሶቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲገዙ የመወሰኑ ወሬ በሚኒስቴር
መሥሪያ ቤቱ በመሰማቱ ሠራተኞች ተደሰቱ፡፡ ሚኒስትሩ በዚህ መሐል ለሙስና መንገድ እንዳይከፈት በአገሪቱ ካሉት አምስቱም የአውቶቡስ
አስመጪዎች የዋጋ ማቅረቢያ በታሸገ ኤንቨሎፕ እንዲያቀርብ አስጠነቀቁ፡፡
***
ከአምስቱም አቅራቢዎች በዝቅተኛ ዋጋ አውቶቡስ ማቅረብ የቻለው ድርጅት አውቶቡሶች አስረክቦ
ሒሳብ ተረከበ፡፡ ያኔ ሚኒስትሩ ስልክ ተደወለላቸው፤ ከወንድማቸው ልጅ!
‹‹ሃሎ…›› አሉ ሚኒስትሩ፡፡
‹‹አጎቴ… አመሰግናለሁ፡፡ በዕቅዳችን መሠረት ትርፉን ለሪዞርቱ ግንባታ ማስኬጃ እናውለዋለን፡፡
ቀሪውን ደግሞ ፈቃዱን ልቀይረውና የቢሮ ዕቃ ባስመጣበት ይሻላል…›› ሌላም፣ ሌላም… ‹‹… ለማንኛውም አንተ አስብበት››